በሪፎርም ቀን በዞን ማዕከልና የዲላ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞ በጋራ በዲላ ከተማ እያከበሩ ይገኛሉ፡፡
“ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት “በሚል መሪህ እየተከበረው ባለው መድረክ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) የተለያዩ የሪፎርም ማሻሻያዎችን በመቅረጽና በመተግበር ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከኪራይ ሰብሳቢነትና ከሙስና አመለካከት የፀዳ አገልግሎት ለመስጠትም ሪፎርሙ ጉሊህ ሚና አለው ነው ያሉት፡፡
የተሻለ አከባቢ ለመፍጠርና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች በንቃት በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ዶክተር ዝናቡ አሳስበዋል፡፡
የዞኑ ትምህርት መምሪያና የዕለቱ መርሃግብር አስተባባሪ አቶ ዘማች ክፍሌ ለህብረተሰቡ ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠትና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር በርካታ ጉድለቶች መኖራቸውን ጠቅሰው የሪፎርም ቀን መከበሩ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አመላክተዋል፡፡
ዘጋቢ፦ እምነት ሽፈራው- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።