የደቡብ  ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት  ኢንዱስቲሪ  ልማት ቢሮ በአምራች ኢንዱስቲሪ  ዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በአዲሱ  አመት  ለማስቀጠል  በትኩረት  እንደሚሠራ  ገለጸ

ቢሮው  የሪፎርም  ቀንን  አስመልክቶ  ከሠራተኞች  ጋር  ውይይት  አካህዷል።

የደቡብ  ኢትዮጵያ  ክልል  የኢንዱስቲሪ  ልማት  ቢሮ  ሀላፊ  ዶ/ር   እንዳልካቸው  ጌታቸው  እንዳሉት  መንግሥት  ሀገራዊ ልማት  ለማፋጠን  ከያዛቸው  ዋና ዋና  ግቦች አንዱ  የሆነውን  የአምራች   የኢንዱስቲሪ  ልማት ዘርፍ በማጠናከር በባለፈው  ዓመት  የተጀመሩ  አመርቂ  ውጤቶችን  በአዲሱ  ዓመት  በአዲስ  ተስፋ  ሰን ቀን  በትጋት መሥራት ይጠበቅብናል  ነው  ያሉት።

በሪፎርም ቀኑ ሁሉም የቢሮው ሠራተኞች እና አመራሮች ተገኝተው አገልግሎት የሠጡ ሲሆን ለአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት ስጦታም ተለዋውጠዋል።

ይህም  የቢሮ ሠራተኛው  እርስ  በርስ  ይበልጥ  በመቀራረብ  ለላቀ  ውጤት ለመትጋት ተነሣሽነትን እንደምፈጥር የገለጹት ደግሞ የቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መንግሥቱ ተክለ ናቸው።

የቢሮ ሠራተኞች የሪፎርሙን ቀን አስመልክተው መደበኛ ሥራቸውን በማከናወን ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።

ዘጋቢ ፡  ወ/ገብርኤል ላቀው- ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን