የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የክልሉን ህዝብ በማስተባበር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው፡፡
በክልሉ ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ ረገድ እየሰራ ያለው ተግባር የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አብራተዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው በክልሉ ያሉ የመልማት አቅሞችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም የተጀመሩ ለውጦችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም በመተግበር የተገኙ ውጤቶች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ በክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ዘጋቢ: አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!