ሀዋሳ: ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ ወዲያ በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበውን አበረታች ውጤት ይበል ማስቀጠል እንደሚገባ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለፁ::
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ከአዲስ ምዕራፍ በወል እሴት ወደ መስፈንጠር” በሚል መሪ ቃል አንደኛ አመት የምሥረታ በዓሉን አክብሯል::
በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት ብሄር ብሄረሰቦች ማንነታቸው እንዲከበር በህግ የተቀመጠውን መብት የመፈፀም ሀላፊነት የተጣለበት ተቋም መሆኑን ገልጸዋል::
ኢትዮጵያ የበርካታ ማንነቶች ሀገር ናት ያሉት አፈ ጉባኤው፤ ህገ መንግስታችን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ይፈቅዳል ብለዋል::
ይሁንና ይህን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ እስከለውጡ ዋዜማ ድረስ ችግሮች እንደነበሩ አስታውሰዋል::
የለውጡ መንግስት ከወሰናቸው እና ምላሽ ከሰጠባቸው ወሳኝ ጉዳዮች መካከል በቀድሞ የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ህዝብ ዘንድ ይነሱ የነበሩ የክልል መዋቅር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ተናግረዋል::
ከምሥታው ጀምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ለመሩት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና ለክልሉ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል::
“አሁን ክልሉ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው:: ጥሩ የአመራር ቅንጅት አለ::” ሲሉ የተናገሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሉ በግብርናው ዘርፍ በ30:40:30 ፕሮግራም የመጣውን ውጤት ይበልጥ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል::
ግቡ ክልል መመሥረት አይደለም፤ ልማትን ማምጣት እንጂ ሲሉም ተናግረዋል::
“የክልሉ ህዝብ እና ምሁራን አመራሩን ሊያግዙ ይገባል:: የመዋቅር ጥያቄ ተመልሷል:: አሁን አመራሩ ልማት ላይ እንዲያተኩር ጊዜ መስጠት ያስፈልጋልም::” ነው ያሉት::
ለእኛ ባይሆንም ለልጆቻችን የምትመች ሀገር ሰርተን ማስረከብ እንደሚገባ ያሳሰቡት አፈ ጉባኤው የፌደራል መንግስትም ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ