በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 29ኛ መደበኛ ጉባኤው እያካሄደ ነው፡፡
የከተማው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፈትለወርቅ በቀለ በጉባኤው መክፈቻ ንግግራቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ የመሠረተ ልማት፣ የጌጠኛው ድንጋይ ንጣፍ፣ የአዳዲስ መንገድ ከፈታና በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አመራሩ ከህዝብ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ በማድመጥና ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ለዘላቂ ልማት በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በጉባኤው የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ“ በአልን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ
ከ 2 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በስኬት ተጠናቋል – የበና ጸማይ ወረዳ አስተዳደር
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም አካሄደ