ሀዋሳ፡ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዲላ ከተማ አስተዳደር ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ኘሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡
ግንባታቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ከበቁ ፕሮጀክቶች መካከል የዲች፣ በኦዳያአ ቀበሌ የተገነባው ድልድይ፣ ለኢንቨስትመንት ተነሺዎች በሁለት ሳይት የተገነቡ 30 የመኖሪያ ቤቶች ተጠቃሾች መሆናቸውን የከተማው ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው አስታውቀዋል፡፡
የትምህርት ስብራት ለመጠገን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችንና ባለ አንድ ወለል ቤተ መጽሐፍት በመገንባት የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል የሚያግዙ ኘሮጀክቶችም መመረቃቸውን ከንቲባው ተናግረዋል።
ለኘሮጀክቶቹ ከ1 መቶ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በምረቃው የተገኙ የዲላ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማው እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በመጎብኘት በከተማው የሚበረታታ የልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፦ እምነት ሽፈራው- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ