በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሬ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ወ/ሮ አካላት በቀለ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች በመቀበል ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ እንዲያገኝ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ ዞን ተወካይ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የኮሬ ዞን ከህብረተሰቡ ለሚነሱት ጥያቄዎች ባለቤት መድቦ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።
የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ምቹ መሠረተ ልማት እንዲኖር ህዝቡ የሚያነሳው ጥያቄ ተገቢነት ያለው መሆኑን በመግለጽ በወረዳና በዞን የሚፈቱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየፈታን ከአቅማችን በላይ የሆነውን ለፌደራል መንግሥት እናቀርባለን ብለዋል።
የኮሬ ዞን ምክትል ኃላፊ፣ የግብርና መምሪያና የመሠረተ ልማትና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ ፣ የግብአት እጥረት በአገር ደረጃ የገጠመ መሆኑን ገልጸው መስኖ ማዘመን የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።
በኮሬ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ጢሞቴዎስ በቀለ ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ ህብረተሰቡ ለሚያነሳው ጥያቄ ተቀናጅተን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ዘጋቢ: ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት በሚደረገው ሂደት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የቀለጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች