ለሀገራዊ ምክክር ስኬት የድርሻችንን እንወጣለን- ተሳታፊዎች

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሀገራዊ ምክክር ሂደት  የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በምክክሩ እየተሳተፉ የሚገኙ  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በምክክር ሂደቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሀገሪቱ ሠላም ጉዳይ  የሁላችንም ጉዳይ እንደመሆኑ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ የድርሻችንን ልንወጣ ዝግጁ ነን ብለዋል።

ኮሚሽኑ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በእኩል በማሳተፍ ሀገር የሁሉም መሆኗን ያመላከተበት ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ያለህብረተሰብ ተሳትፎ  ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበንበታል ብለዋል።

አለመግባባትን በምክክር ለመፍታት መመካከራችን ሁነኛ መፍትሔ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ- ከሆሳዕና ጣቢያችን