የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ እየተሳተፉ ያሉ ወጣቶች መካከል ወጣት ሮዛ ሸምሱ፣ ታምራት ይልማ እና ማርታ ገብሩ ምክክሩ የሚገጥሙ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ መልካም አጋጠሚ የፈጠረ ነው ብለዋል::
ወጣቶቹ ለሃገር የመፍትሄ ሐሳብ እንዲያመጡ እድለ የፈጠረ ውይይት መሆኑን ወጣቶቹ አመላክተዋል::
ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት በሰከነ መንፈስ፣ በእውነት እና በእውቀት ላይ ተመስርተው ወጣቶች መመካከር እንዳለባቸውም ወጣቶቹ መክረዋል::
በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ግጭቶች ወጣቶችን እየቀጠፉ ስለነበር ምክክሩ ወጣቶች ያላቸውን ተስፋ እንዲያለመልሙ ያስቻለ እንደሆነም አስተያየታቸውን የሰጡ ወጣቶች ጠቁመዋል::
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ