እርቀ ሰላም “ለአንድነት፤ ለአብሮነትና ለወንድማማችነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው::
የሰላም እጦቱን ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ የከተማዉ ህዝብ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተጠቁሟል።
በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ከሊል፣ የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪ መልዓከ ህይወት ቀሲስ ንጉሴ ባወቀን ጨምሮ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች፣ የአጎራባች ወረዳዎች፣ የከተማው ነዋሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ: ናስር ጀማል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።