ሀዋሳ፡ ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአሪ ዞን ከገሊላ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ “ተስፋ ያለው ባለራዕይ በጎ አድራጎት ማህበር” አባላት በደቡብ ኣሪ ወረዳ የከተማ ፅዳትና ችግኝ ተከላ አከናውነዋል ፡፡
የደቡብ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛው ኃይሌ ማህበሩ ላደረገው በጎፈቃድ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
በኣሪ ዞን የገሊላ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ኤልያስ ተስፋ ያለው ባለራዕይ በጎ አድራጎት ማህበር እያከናወነ ያለው ተግባር የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡
ማህበሩ ሕጋዊ ዕውቅናን ካገኘ በኀላ የወጣቱን ግንኙነት በማሳለጥና የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለማቃለል እየሠራ መቆየቱን የማህበሩ አስተባባሪ ወጣት መርደክዮስ ዮሐንስ ገልፀዋል፡፡
በበጎ አገልግሎቱ ከተሳተፋ የማህበሩ አባላት መካከል ወጣት ተስፋዬ ተክሌና ውድዬ እሳቱ በጋራ እንደገለፁት የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋጥ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረው በነበራቸው ቆይታ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጣቸውን አስረድተዋል ፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ- ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።