በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 180 ኢንቨስትመንት መሳብ ተችላል- ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የፌዴራል የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት አስፈጻሚዎች የጋራ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 180 ኢንቨስትመንቶች ወደ ክልሉ እንደመጡ ጠቁመው ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ክልሉ በድንጋይ ከሰል፣በወርቅና በሌሎች ማዕድናትም የበለጸገ መሆኑን አንስተው ክልሉ ለእንቨስትመንት አሁንም አመቺና ብዙ አማራጮች አሉት ነው ያሉት።

የኢፌዴሪ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ኢትዮጵያ ተወዳዳሪና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆን ዕድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።

አሁንም በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በየአካባቢው ያለውን ዕምቅ አቅም በአግባቡ በማስተዋወቅ ለጋራ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ለማሳለጥ መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ግዴታ ነው ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ዞኑ ለኢንቨስትመንት ምቹ እንደሆነ አንስተው በተለይ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ጥራት ያለውን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በ2016 በጀት አመት 27 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቦ 6ሺህ ቶን በመጋዝን ውስጥ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ ከቤንች ሸኮ ዞን የተመረጡ የኢንቨስትመንት ቦታዎች እንደሚጎበኙ የወጣው መርሃግብር ያመላክታል።

ዘጋቢ፡ ወሰኑ ወዳጆ- ከሚዛን ቅርንጫፍ