ሀዋሳ፡ ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከወከሉ ተመራጮች አጀንዳን ለማሰባሰብ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ብሔራዊ ምክክር ዓላማው ብሔራዊ እርቅን ማምጣት መሆኑን ጠቁመው ተሳታፊዎች ውይይቱ እስከሚያልቅ በንቃት በመሳተፍ የሀገራዊ ምክክሩን ዓላማ በማሳካታ የሀገሪቱን ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በውይይት መድረኩ በክልሉ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ከሃይማኖት ተቋማት፣ሲቪክ ማህበራት፣ከንግዱ ማህበረሰብ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ሴቶች፣አካል ጉዳተኞች፣የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ቋሚ ኮማቴ አባላትን ጨምሮ ከሶስቱም የመንግስት አካላት የተውጣጡና ሌሎችም አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
ከውይይት መድረኩ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምክክር የሚሆኑ ወሳኝ ግብዓቶች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:አማኑኤል አጤቦ- ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ