የወላይታ ዞን ምክረ ቤት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ እየሠራ እንደሚገኝ ገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወላይታ ዞን ምክረ ቤት የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሰት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አኳያ ምክር ቤቱ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገር የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎችን ከማጠናከር አኳያም በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሀላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መቆየቱን ገልጸዋል።

የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አፈ ጉባኤዋ አመላክተዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህዝቡ የሚያነሳቸው የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በተደረገው ጥረት አበረታች ለውጥ መታየቱን አብራርተዋል።

የህግ የበላይነት ከማስከበር ረገድ የህዝቦችን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚወጡ ህጎችና አሰራሮችን ተፈጻሚ ለማድረግ የምክር ቤት አባላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

በታችኛው መዋቅር የሚገኙ ምክር ቤቶችን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ ከዋካ – ቅርንጫፍ