በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል- የገሊላ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዮኒት

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሌማት ትሩፋት ሥራዎች በተለያዩ ዘርፎች በማደራጀት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በኣሪ ዞን የገሊላ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዮኒት አስታወቀ።

የገሊላ ከተማ አሰተዳደር ግብርና ዮኒት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተሾመ እንደገለፁት በከተማው የተለያዩ የሌማት ትሩፋት መንደሮችን በማደራጀት እየተሠራ ብለዋል፡፡

በተለይም በወተት መንደር 9 ማህበራት ተደራጅተው 432 የአከባቢና 108 የውጪ ዝርያ ያላቸው ላሞችን በማደለብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም 1 ሺ 80 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

አክለውምበእንቁላል መንደር 16 ማህበራት ለማደራጀት ታቅዶ 12 የተሰራ ሲሆን 679 ዶሮ ማርባት መቻሉን አንስተዋል፡፡

ኃላፊው በማር መንደር 15 ዘመናዊ፣ 10 የሽግግርና 132 ባህላዊ ቀፎዎች ተለይተው እየሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።በተመሳሳይ በሥጋ መንደር 11 ለማደራጀት ታቅዶ 4 በማደራጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ መቻላቸውን ገልጸዋል።

አቶ መልካሙ የክሞ በገሊላ ከተማ የ02 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በ2004 ዓ.ም ሁለት የተሻሻሉ ላሞችን በ12 ሺህ ብር ገዝተው በማርባት ዛሬ ላይ 25 ላሞችን ማድረስ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ በሳምንት 2 ጊዜ ለራሳቸው ምግብ ቤትና ለሌሎች በማከፋፈል ተጠቃሚ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

አሁን ላይ 2 ሚሊየን ብር ካኘታል ማፍራታቸውንና በቀጣይም ትራክተር ገዝተው ለማረስና በዶሮ እርባታ ዘርፍ ለመሰማራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ከተማ በየነ- ከጂንካ ጣቢያችን