አስተያየታቸውን ከሰጡን የከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ማንደፍሮ ታንና አብነት እያሱ፤ ከዚህ ቀደም ሰለከተማ ግብርና እንደማያውቁና በመሸመት ብቻ ይተዳደሩ እንደነበር አሰታውሰው ዛሬ ላይ በጓሮአቸው ድንች፣ ጥቅል ጎመን፣ የደጋ በቆሎና ሌሎችንም በማምረት ከውጭ ሸምተው ከመጠቀም ተላቀው ወጪያቸውን መቀነስ መቻላቸውን ገልጸዋል።
በከተማ ግብርና መሳተፋቸው አሁን እየታየ ያለውን የኑሮ ጫና መቋቋም እንዳስቻላቸውም ጠቁመዋል።
የገሊላ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዮኒት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተሾመ፤ ከተማው አርሶአደሩንም ከተማ ነዋሪውንም አቅፎ የያዘ እንደመሆኑ በከተማ ግብርና ምግባቸውን ከጓሮአቸው እንዲያገኙ በየጓሮአቸው ባለው ትንሽ መሬት የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን እንዲያለሙ ግንዛቤ በመስጠት እንዲያመርቱ እያስቻለ ሲሆን በዚህም አብዛኛዎቹ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ