ጉባኤዉ በሁለት ተከታታይ ቀናት ቆይታቸዉ የወረዳውን የ2016 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትና የ2017 ዕቅድ፣የአስፈፃሚ መሰሪያ ቤቶች እና የፍርድ ቤት የዓመቱ አፈፃፀምና የ2017 ዕቅድ ተገምግሟል።
በወረዳው የ2016 በጀት አመት አስተዳደር ምክር ቤት አፈፃፀምና የ2017 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ለተነሱ ሐሳቦች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ አልጋጋ ባልንሴ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ ገቢ አሰባሰብ ለይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ለአፈፃፀሙ ስከታማነትም የምክር ቤት አባላት ህብረተሰቡን የማስተባበር ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ምክር ቤቱ የ2017 በጀት አመት ሥራ ማስፈፀሚያ 2መቶ 69ሚሊዮን 1መቶ 27ሺህ 5መቶ 3 ብር ረቂቅ በጀት ቀርቦላቸዉ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
የወረዳዉ ዋና አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤን ጨምሮ ሌሎች በተጓደሉ ካቢኔ አባላትና ቋሚ ኮሚቴዎች ቦታ ሹመት ቀርቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።
ዘጋቢ ፡ ገጶስ አየለ ከጂንካ ቅርንጫፍ!!!

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ