የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሴክቶራል ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሴክቶራል ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
ሀገራችን የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን ተግባራዊ እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የክልሉ ር/መ አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በጉባኤው የቢሮው የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 ዕቅድ ላይ ውይይት ይካሄዳል።
ዘጋቢ፡ ብሩክ ፋንታ
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ