በገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች ድጋፍ አደረጉ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች ከ35ሺ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
በገዜ ጎፋ ወረዳ የደረሰውን ያልታሰበ አደጋ በማስመልከት “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል የመ/ቤቱ ሰራተኞች ከወር ደሞዛቸው በመቀነስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የደቡብ ሬዲዮና ተሌቪዥን ድርጅት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉጃ ጉሜ አስረድተዋል።
የቅርንጫፍ ሬዲዮ ጣቢያው ሰራተኞች አደጋውን በማስመልከት ከደሞዛቸው በመቀነስ 35ሺ 200 ብር ለዚሁ አላማ በተከፈተው አካውንት ገቢ ማድረጋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።
በቀጣይም ለሚደረገው ማንኛውም ድጋፍ አጋርነታቸውን በተግባር እንደሚያሳዩም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ አሰግድ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ