ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑና የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ተግባራት በትኩረት ሊፈጸሙ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑና የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ተግባራት በትኩረት ሊፈጸሙ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) አመራሩ ሀገራዊ ዕድገትን የሚያፋጥኑና የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ተግባራትን በትኩረት መፈፀም እንዳለባቸው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ ገለጹ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ የመንግሥት  ሥራ የአፈፃፀም ግምገማና የፓርቲ ምዘና መድረክ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ማዕረግ የማህበራዊ  ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ እንደገለፁት የሕብረተሰቡን  የልማት ተጠቃሚነት  ለማረጋገጥ  በየዘርፉ የተከናወኑት ተግባራት በመገምገም  ጥንካሬና ጉድለትን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጡን ገልፀዋል ፡፡

በጤና፣ በትምህርት፣ በመስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት፣ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች እንዲሁም በወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ የታቀዱ  ሥራዎች ሀገራዊ እድገትን እንዲያፋጥንና የህብረተሰቡን  ችግር  እንዲፈቱ  አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበት ዶክተር አበባየሁ አንስተው ለዘላቂነቱ ሁሉም የድርሻቸውን  ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

በአፈፃፀም ግምገማ የተነሡ ሀሳቦችን በመተግበር የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የማህበረሰቡን  ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሚሠሩ የመድረኩ ተሳታፊ አመራሮች ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን