ሀዋሳ፡ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የመንግስት ሠራተኛው የሚስተዋሉ የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በመቀረፍ ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቁረጠኝነት ማገልገል እንዳለበት ተመላክቷል።
በደቡብ ኢትዮጰያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወርዳ የመልካም አሰተዳደር ንቅናቄ መደርክ የህዝብ ተወካዮችና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በሀና ከተማ ተካሂዷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረዳው እየተበራከተ የመጣውን የመልካም አሰተዳደር ችግር መቅረፍ እንደሚያስፈልግ በመድረኩ በስፋት ተነሰቷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አጉ ደባን እንደገለፁት በወርዳው የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የሚስተዋሉ የፀጥታ፣ የመንግድ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የማብራትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ሥራዎች በወቅቱና በታቀደው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አመራሩና ሲቭል ሰርቫንቱ በቁርጠኝነትና በታማኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ወረዳው እንደ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድና ሁለትን ጨምሮ የማጎ ብሔራዊ ፓርክና ሌሎች ሰፋፊ ሀገራዊና ክልላዊ ፕሮጀክቶች መገኛ እንደመሆኗ በተለይ በአከባቢው ፀጥታ ጉዳይ ላይ የዞን እና የወርዳ አመራር፣ ህብረተሰቡና የሚመለከተው አካል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
የሣላማጎ ወርዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ኡሉሉ ቻረነሊ በወረዳው የሚስተዋሉ የልማትና መልካም አሰተዳደር ችግሮችን በመለየት በተለይ ለመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት የሆኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ ገልፀው የህብረተሰቡ ጥያቄ በሆኑ ያልተመለሱ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ዙሪያ ከዞንና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይፈታል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ: ግዳጁ ጎርጊ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ