በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 31ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 09/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አድማሱ ማሴቦ በመግቢያ ንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት ምክር ቤቶች የህዝብን  ሉዓላዊነት ከማስከበር ባሻገር  የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት  ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራሉ ።

መንግስት ያጎናፀፈውን በልዩ ወረዳ የመደራጀት መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቅርቡ በልዩ ወረዳው የጠምባሮ ልማት ማህበር መቋቋም  ከተከናወኑ ተግባራት አንዱ  መሆኑን የጠቆሙት ዋና አፈ-ጉባኤው  በቀጣይም የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማደራጀት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ከተረጅነት ለመላቀቅ  የሚያስችሉ ስራዎች ከአመራሩና ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ስለመሆናቸውም ዋና አፈ-ጉባኤው አመላክተዋል።

ጉባኤው የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የበጀት ዓመቱን የስራ አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ የስራ ዘመን ዕቅድ ላይ ውይይት  ያደርጋል።

 ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ጉባኤው የ2016 አፈፃፀም ሪፖርት በመገምገም   የ2017 የስራ ዘመን ጠቋሚ ዕቅድና ማስፈፀሚያ  በጀት  ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ፡ አማኑኤል አጤቦ ከሆሳዕና ጣቢያችን