በክረምት የሚተገበሩ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት የበርካታ ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እየፈታ መሆኑ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክረምት የሚተገበሩ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት የበበርካታ ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እየፈታ መሆኑ ተገልጿል።
የጂንካ አጠቃላይ አጠቃላይ ሆስፒታል “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ነፃ የክረምት በጎ ፈቃድ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።
ሲ/ር ባንችወሰን አሰፋ ሆስፒታሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የደም ልገሳን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ቤታቸው የሚታደስላቸው ወ/ሮ አልማዝ ጎመጆ ደሳሳ ሳር ቤታቸው ዝናብና ፀሐይ ስፈራረቅ በጣም ተጨንቀው ይጠለሉ እንደነበረ ገልፀው በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታሉ ለሚያደርግላቸው በጎ ሥራ አመስግነዋል።
የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ብርክታዊት አሰፋ ሆስፒታሉ ከመደበኛ የህክምና አገልግሎት ባሻገር በበጎ ተግባር በስፋት እየተሳተፈ ይገኛል ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
በሥራው የተሳተፉና ያስተባበሩ አካላትም በተግባራቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው ድጋፍ ለሚሹ አካላት ቀጣይነት ያለው በጎ ሥራ እንደሚደረግላቸውም ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማጠናከር ክልላዊ አንድነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ