በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት ከ1 ቢሊዬን 497 ሚሊዬን ብር በላይ በጀት በማፅደቅና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጉባኤውን አጠናቀቀ
የህዝብና የመንግሥት ውስን ሀብትን በአግባቡ በመምራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬ አሳስበዋል ፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በጥንካሬና በድክመት የታዩ አፈፃፀሞች ላይ አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተው በግብርና ፣በኢንቨስትመንት እንዲሁም በመሠረተ ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ፡፡
ከሕብረተሰቡ የሚሰበሰቡና ከመንግሥት የሚመደበው ውስን በጀት በቁጠባ ለታለመለት ዓላማ በማዋል የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
የዞኑ የ2017 በጀት ዓመት ሥራ ማስፈፀሚያ 1 ቢሊዬን 497 ሚሊዬን 337 ሺህ 317 ብር ጸድቋል ፡፡
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገልፀው የውስጥ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ በጀቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፌጉባኤ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬ እንደገለፁት ውስን ሀብትን በአግባቡ በመምራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል ፡፡
ምክር ቤቱ የቀረቡለትን ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል ፡፡
ዘጋቢ – ተመስገን አሰፋ-ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሀን ለመሻገር በተሰሩ ተግባራት ውጤት ማምጣት መቻሉ ተገለጸ
የኅብር ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የኣሪ ዞን አስተዳደር ገለጸ
የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሐሣብ በማዕከላዊ ኢትዮያውያ ክልል ሣጃ ክላስተር እየተከበረ ነው