የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ እንደገለፁት ምክር ቤቱ በህገመንግሥቱ በተሰጠው ኃላፊነት የህግ አስፈፃሚውና የህግ ተርጓሚው ሥራ በመቆጣጠርና በመከታተል ለዜጎች ተጠቃሚነት በርካታ ተግባራት አከናውኗል፡፡
የዜጎችን ሠላምና ደህነት ለማስጠበቅ እየተሠሩ ያሉ መልካም ጅምሮችን ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በማህበራዊና በኢኮኖሚ እንዲሁም በህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፎች ለዜጎች ፍትሐዊና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት የምክር ቤቱ አባላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አፈጉባኤዋ አሳስበዋል፡፡
ምክር ቤቱ በሁለት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-