በዞኑ በጀት ዓመቱ በልማትና መልካም አሰተዳደር ሥራዎች ላይ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውም ተጠቁሟል።
የ2016 በጀት ዓመት የጌዴኦ ዞን አሰተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ የምክር ቤቱ አባላት 4ኛ ዙር 25ኛ መደበኛ ጉባኤ በዲላ ከተማ በማካሄድ ገምግሟል።
በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ያስጀመሩት የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ምስጋና ዋቃዮ፤ በ2016 በጀት ዓመት በዞኑ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያላቸው የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተሠርተዋል ብለዋል።
የዞኑን አስተዳደር የ2016 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በግብርና ሥራዎች ላይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በእንሰት፣ በቡና፣ በተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ በማር፣ ዶሮ እርባታ እና ሌሎች ተግባራት ላይ አመርቂ ሥራዎች ሰለመሠራታቸው ተገልጿል።
አርባ ሚሊዮን 1 መቶ 57 ሺህ በላይ እንሰት ለመትከል ታቅዶ ከ43 በሚሊየን 3 መቶ 19 በላይ መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን ቡና ተከላ ከዕቅድ በላይ ተሳክቷል ብለዋል።
የቡና ጥራትን አስጠብቆ በገበያው ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ሰፊ ሥራ እንደሚጠበቅም አንስተዋል።
በትምህርት፣ ውሃና ማዕድን፣ በጤና፣ በኢንተርኘራይዝ፣ በገቢ፣ በመንገድ መሰረተ ልማት በተለይ በከተማ አዳዲስ የመንገድ ከፈታ ሥራ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና ሌሎች ሥራዎች ላይ አበረታች ውጤቶች እየታዩ ቢሆንም ጠንከር ያለ ሥራ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በትምህርት ሥራ ላይ የጌዴኦ ልማት ማህበር ት/ቤቶችን በማስገንባት ያደረገውን ሥራ ያደነቁት አስተዳዳሪው፤ እንደዚህ ዓይነት መልካም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁላችንም በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በጤናው ዘርፍ ላይ የጤና መድህን ገቢ በአግባቡ ሰብሰቦ ያለመጠቀም ችግሮች እንዲሁም በገቢ ላይ ታክስ ስወራ፣ የቫት፣ የቲኦቲና የግብይት ደረሰኝ ያለመሰጠት ችግሮች እየተስተዋሉ መሆናቸውን ጠቁመው ይህንን ለመቅረፍ በጋራ ተቀናጅን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ዘጋቢ: ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ