የብልፅግና ፓርቲ ስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ገቡ
ሚንስትሯ ወደ ሆሳዕና ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሆሳዕና ቆይታቸው 2017 በጀት ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ መስኮች ላይ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ካቢኔ አባላት ጋር ዉይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከሚኒስትሯ ጋር የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች እና የማኔጅመንት አባላትም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ጀማል የሱፍ
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!