በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባደረጉት ንግግር በክልሉና በዞኑ አስተዳደር ወደስራ የገባው የሬዲዮ ጣቢያው የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የመለሰ ነው ብለዋል።
የማሻ ኤፍ ኤም 103.8 ከማዝናናትና መረጃ ከመስጠት በተጨማሪ አካባቢው ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ የሚማርኩ መልክዓ ምድርና የመስህቦች ባለቤት በመሆኑ ለአለም ማስተዋወቅ እንደሚገባውም አንስተዋል።
ክልሉ ሚዲያ ኔትወርክ በማደራጀት ወደስራ የማስገባት ሂደት ላይ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው የህዝብን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲረጋገጡ አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ የሬዲዮ ጣቢያው ለህብረተሰቡ ተስፋ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በምረቃው ፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ እና ሌሎች የፌደራል፣ የክልል፣ የሸካ ባህላዊ አስተዳደር፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለድርሻ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ልጃለም ማሞ – ከማሻ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ