የተጀመሩ ልማቶችን በማስቀጠል የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ማዘጋጃ ቤቶች ቅኝጅታዊ አሰራሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ

የተጀመሩ ልማቶችን በማስቀጠል የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ማዘጋጃ ቤቶች ቅኝጅታዊ አሰራሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀምና የ2017 ዕቅድ የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

የግምገማውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አበባዬሁ ኢሳይያስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማው እየታዬ ያለው አበረታች ለውጥ የቅንጅታዊ አሰራር ውጤት  እንደሆነ ገልጸው ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በከተማው የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ያለ ህዝብ ተሳትፎ እውን ማድረግ ስለማይቻል የህዝብን ተሳትፎ በማጎልበት የተሰራው ሥራ ልምድ የተወሰደበት እንደ ነበረ የገለጹት ደግሞ የከተማው ዋና ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን ናቸው።

እምቅ የመልማት ዕድል ያለውን ይህን ከተማ አልምቶ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ ሁሉም እንዲረባረብ አሳስበዋል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም በአዲሱ ስትራቴጂክ ፕላን መሠረት ወደ ከተማ የተካለሉ ማስፋፊያ አካባቢ ማህበረሰቡን በማወያየት 2 መቶ ሄክታር በሚሆን መሬት የትግበራ ሥራ መከናወኑ ተገልጿል።

በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን ኦዲት በማድረግ 31 ሺህ ካሬ ሜትር ከተገኘው መሬት መመሪያን ተከትሎ ከ20 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነውን ወደ መሬት ባንክ ማስገባት መቻሉም ተመላክቷል።

ፕላኑን መሠረት ባደረገ መልኩ ኅብረተሰቡን በማስተባበር ከ19 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ መንገድ ከፈታ መደረጉ አበረታች ውጤት መመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን በኮሪደር ልማት ዘርፍ ተስፋ ሰጪ አፈፃፀም ታይቷል ነው የተባለው።

በበጀት ዕመቱ በማዘጋጃ ቤቱ የተመዘገበው ውጤት በዞኑ ካሉት መዋቅሮች የተሻለ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በተመዘገበው ዉጤት ሁሉም ሳይዘናጋ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ  የድርሻውን እንዲወጣ የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ታምራት አሳስበዋል።

ዘጋቢ:  አማኑኤል ትዕግስቱ  –  ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን