የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በአደጋው ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች የተሰማቸውን ልባዊ ሐዘንም በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ር/መስተዳር ማዕረግ የዲላ ክስተር አስተባባሪና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር- ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ