ለህዝቡ ሠላምና የልማት ተጠቃሚነት ሁሉም ቀጣይነት ያለው ትኩረት ማድረግ እንዳለበት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ሎስንዴ ሎኛሱዋ አሳሰቡ

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በዲመካ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ ጉባኤውን የጀመረው በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊን ፀሎት በማድረግ ነው።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አዲስ ሽግግር ምክር ቤት አባላትን ለጉባኤው አቅርቦ በሙሉ ድምጽ ፀድቆ አዳዲስ የምክር ቤት አባላትም ቃለ መሐላ በመፈፀም ነው መደበኛ ጉባኤው የተጀመረው።

የህዝቡ ሠላም ተጠብቆ የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት በመክፈቻ ንግግራቸው ያሳሰቡት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ሎስንዴ ሎኛስዋ ናቸው።

ምክር ቤቱ በሚኖረው የሁለት ቀናት ጉባኤ የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምን ማድመጥና ማፅደቅ፣ የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶ ማጽደቅ የሚሉና በ12 አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን