“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በዳሰነች ወረዳ የችግኝ ተከላ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞ በዳሰነች ወረዳ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞ በዳሰነች ወረዳ የአርንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የዳሰነች ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የውሃና ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ናኩዋ በንግግራቸው እንደገለፁት የአርንጓዴ አሻራ ለማኖር ዳሰነች ወረዳን መርጣችሁ ስለመጣችሁ የክልሉን አመራርና ሠራተኞች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የዳሰነች ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘካርያስ አንበሰ በበኩላቸው እንደ ወረዳ 70 ሺህ 900 በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ይህም የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አረጋ አርብቶ አደሩ አከባቢ በአብዛኛው በድርቅ የሚጠቁ በመሆናቸው ይህ እንዲያገግም በተለይም ለምግብነት የሚያገለግሉ ችግኞችን በመትከል ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት እየተሠራ ነው ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ሀብቴ እንደ ክልል የታቀደውን 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብሎም እንደ ሀገር የተያዘውን 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ተከላ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል እየተሠራ ሲሆን የክልሉ መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ በዳሰነች ወረዳ 10 ሺህ ችግኝ እንደሚተከል ተናግረዋል።
እንደ ክልሉ መስኖና ቆላማ አከባቢ ቢሮም 40 ሺህ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች እንደሚተከሉ ኃላፊው ተናግረዋል።
በተከላው የተሣተፉ ሰራተኞችና አርብቶ አደሮችም ችግኝ መትከል የመሬት መራቆትን ከማስቀረት ባለፈ ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ እንዲዘንብ እንዲሁም የመሬት መንሽራተት አደጋዎችን የሚከላከል በመሆኑ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው።
በተከላው ለአርብቶ አደሩ ኢኮኖሚ አሰፈላጊ የሆኑ ለምግብነት የሚያገለግሉ ችግኞችን መትከላቸውንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ