የሆሳዕና ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ለ6ኛ ዙር በድፕሎማ፣በመጀመሪያ ድግሪና በሁለተኛ ድግሪ በተለያዩ የስልጠና መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 2ሺ783 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከተማራቂዎቹ 1ሺ87 ወንዶች ሲሆኑ 1ሺ699ኙ ሴቶች መሆናቸውን ከኮሌጁ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የምረቃ መርኃግብሩን በእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት የከፈቱት የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ ኮሌጁ በሀገሪቱ በዕውቀትና ክህሎት የበቃ የሰው ኃይል በመፍጠር በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ መሆንን ዓላማ አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በምረቃ መርኃግብሩ ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት እንስትትዩት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃሌፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል መንታሞ- ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።