ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በስፍራው ተገኝተው አፅናንተዋል፡፡
ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ሰው ለማዳን በሄዱበተ ውድ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ሃዘን ልብ ሰባሪ ነው ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው እስካሁን የቤተሰብ አባል ይመጣል እያሉ የሚጠብቁ ሰዎች መኖራቸውን አንስተው አደጋው ልብ ሰባሪ እንደሆነ ገልፀው ኢትዮጵያውያን ላደረጉት ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ተጎጂዎችን በዘላቂነት ማቋቋም ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
የመቶዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓም ማለዳ በጎፋ ዞን ሻቻ ኪንቾ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዴሊ በተባለ ስፍራ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ
More Stories
አርብቶ አደሩን ከእንስሳት ሀብት ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእንስሳት ኤክስፖርት ማዕከላት እንደሚያስፈልጉ ተጠቆመ
በጌዴኦ ዞን የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ