546 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴን ማክሸፍ ተችሏል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
ሀዋሳ፡ ሀምሌ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉን ሠላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ 546 ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን አላማ ማክሸፍ መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ዙር 4ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ተገኝተው የክልሉን የ2016 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርታቸውም የክልሉን ሠላም ለማወክ አላማ አድርገው የተነሱ 546 ማህበራዊ ሚዲያዎችን መግታት ተችሏል ብለዋል።
ሚዲያዎቹ ክልሉ እንዳይረጋጋ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን በተደረገ ክትትል መረጋጉጡን አስታውቀዋል።
አክለውም በክልሉ የወንጀል መጠን 10 በመቶ ለመቀነስ ታቅዶ 11 በመቶ መሠራቱን አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ