ባለፈው በጀት አመት 10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 በጀት አመት 10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የበጀት አመቱን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛል።
በሪፖርታቸውም በ2016 በጀት አመት በክልሉ 12 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሠብሠቡን ገልጸዋል።
አፈፃፀሙ 87 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ