የመንግስትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በማሳየት ቅንጅታዊ አስራርን በመከተል ውጤታማ ሥራ መሰራት መቻሉ ተጠቆመ
የመንግስትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በማሳየትና ቅንጅታዊ አስራርን በመከተል ውጤታማ ሥራ መሰራት መቻሉን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ አስታወቀ።
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ ተካሂዷል።
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ የልማት ዕቅድ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በሬዲዮ፣ በቴሌቭዥን፣ በሚዲያ ቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና ሌሎችም ዘርፎች የተያያዙ ዕቅዶችን ከማሳካት አንፃር በተሻለ ሁኔታ መፈፀም መቻሉን ገልፀው ይህም እንደ ተቋም አፈፃፀሙን 91 ነጥብ 06 በመቶ ሊደርስ ችሏል ብለዋል።
የመድረኩ ተሣታፊዎችም በዕቅዱ መነሻ እንደ ተቋም ለሚዲያው ሥራ ውጤታማነት ከዚህ ቀደም የነበሩ በርካታ ችግሮችን በመቅረፍና በቅንጅት በመምራት የመጣ ውጤት መሆኑን ገልፀው እንደዝሁ የሚዲያውን ሚና የሚጎትቱ ተግባራት ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አንስተዋል።
አክለውም ቅርንጫፉ 3 ዞኖችን ይዞ ሽፋን እንደመስጠቱ መጠን የምዲያ ሽፋን ተደራሺነቱን በፍትሐዊነት በማዳረስ በሁሉም አከባቢ ያሉ የልማት ውጤቶችን ከማስተዋወቅና ደካማ ጎኖችን ከማሳየት አንፃር ቀሪ ሥራዎችን በመስራት የሚስተዋሉ አንዳንድ የግብዓት ችግሮችን በቅንጅት መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉዋስ አቲሳ እንደ ተቋም የመጡ ውጤቶች የሁሉም የቅንጅት ውጤት በመሆኑ ለመጣው ውጤት በተቋሙ ስም አመስግነው አስራርን በመከተል ባለሙያን በማሰልጠን የአቅም ክፍተቶችን የመሙላት ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
በቀጣይም ባለሙያው ጉድለቶችን በማረም ከዚህ በበለጠ ሊስራ ይገባል ሲሉ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
የሚዲያው ሥራ ከዚህ በተሻለ እንዳይፈፀም ማነቆ የሆኑ ችግሮችንም ደረጃ በደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመናበብ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ተቋም በመጣው ውጤት መነሻ በማድረግ በግለሰብ ደረጃ የተሻለ ውጤት ያመጡ ስራተኞችን የማበረታታትና የትምህርት ዕድልም ጭምር እንደሚያገኙ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በክረምት በጎ ተግባር ሰራተኛው በፍቃደኝነት ከደሞዛቸው ደብተር ለመግዛት ቃል በመግባትና የ2017 ዓ.ም ተቋሚ ዕቅድ ቀርቦ በጋራ መግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።
ዘጋቢ: አርኝሮ አርሻል – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ