ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን ጠቃሚ ባህሎችን በማጠናከር ለሀገር ሠላምና ልማት ማዋል እንዳለባት በሀዲያ ዞን የሚገኙ የባህል ሽማግሌዎች ተናገሩ

ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን ጠቃሚ ባህሎችን በማጠናከር ለሀገር ሠላምና ልማት ማዋል እንዳለባት በሀዲያ ዞን የሚገኙ የባህል ሽማግሌዎች ተናገሩ

በዞኑ ጎምቦራ ወረዳ የባሕላዊ የምርቃት ኘሮግራም ተካሂዷል ።

ባሕል የአንድን ህዝብ ፣የአኗኗር፣ የአመጋገብ፣ የአለባበስ የአጋጌጥና ወዘተ መገለጫ ሲሆን የአንድ ሕዝብ አንጡራ ሀብቱ ነው ።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሀገር ባሕል ሽማግሌዎች የሚያደርጉት ባህላዊ የምርቃት ስነ- ስርዓት ዋና አላማዉ ለሀገር ሰላም፣ አንድነትን የሚያመጣ ለአከባቢው ልማት ያለው ፋይዳ ከፈተኛ ነው ተብሎ በበርካቶች ይታመናል ፡፡

የሀዲያ ብሔር ከጥንትም ጀምሮ የበርካታ ባሕላዊ እሴቶች ባለቤት ሲሆን ከዚህም ዉስጥ አንዱ የባሕላዊ ምርቃት ስነ- ስርዓት ነው።

በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ በተካሄደው ባህላዊ ምርቃት ኘሮግራም ላይ ካነጋገርናቸው የባሕል ሽማግሌዎች መካከል አዲል ደዳች ፣በርከፈት ታድዬ ፣ቦያሞና አንጃንቾ ቡላ ቆሎሌ እንዳሉት በሀዲያ ብሔር ትውልድ እንዲባረክ፣በሀገሪቱ ልማት ፣ሰላምና አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር የባሕል ሽማግሌዎች ምርቃት እንደሚካሄድ ገልጸዋል ።

ጠቃሚ ባህሎችን ጠብቆ ለትውልድ ማሸጋገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ መሆኑን የገለጹት የባህል ሽማግሌዎቹ ትውልዱ በትምህርትና በሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ እንዲሆኑ ታስቦ የምርቃት ኘሮግራም እንደተዘጋጀም ተናግረዋል ።

ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን ጠቃሚ ባህሎችን በማጠናከር ለሀገር ሠላምና ልማት ማዋል እንዳለባትም የባህል ሽማግሌዎች ተናግረዋል ።

የጎምቦራ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ አበበ በበኩላቸው መንግሥት ለሀገር ሰላምና አንድነት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ባለበት ወቅት ይህ መልካም የሆነው ባህላዊ ምርቃት መደረጉ የህብረተሰቡን አንድነት የሚያጠናክር ነዉ ብለዋል ።

የጎምቦራ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም ጎበና ምርቃት በመሰረቱ ሰላምንና አንድነትን የሚያሳይ ብሎም ለአከባቢ ልማት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዘጋቢ : ታምራት አለሙ ከሆሳዕና ጣቢያችን።