የኣሪ ህዝብ ልማት ማህበር የውስጥ አደራጀቱን በማጠናከር የህዝቡ የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት ጠንክር እንደሚሠራ አስታወቀ
ልማት ማህበሩ ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።
መረዳዳትና መተጋገዝ ፣ወንድማማችነት ፍቅር፣ጠንካራ አቋም፣አንድነት፣ ፍትሐዊነትና ደንብን ማክበር የሚል እሴት ያለው የኣሪ ህዝብ ልማት ማህበር በ2011ዓ/ም ተቋቁሞ የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ማህበር እንደሆነ ታውቋል።በአሁን ወቅት ከ17ሺህ በላይ አባላት እንዳሉትም ተገልጿል ።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የኣሪ ልማት ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም አታ እንደገለፁት ልማት ማህበሩ በህዝቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ከመንግስት ጎን በመቆም እየሠራ ይገኛ፤ ይህንንም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ማህበሩ የጀማመራቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን በማስቀጠል በቀጣይ በተሻለ መልኩ አቅም በየአካባቢው በልማታዊ ሥራዎች ተሳትፎውን ያደርጋል ሲሉም አቶ አብርሃም አስታውቀዋል ።
የኣሪ ህዝብ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ወይካ ልማት ማህበሩ በበጎ ሥራዎች፣በጤና፣በትምህርት እና መሰል ልማት ሥራዎች በስፋት መሳተፉን አብራርተዋል ። ይህ ተግባርም በተለያየ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም እንዲሁ።
በ2017 ዓ/ም ከ3 መቶ ሺህ በላይ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ስለ ማህበሩ ግንዛቤ ንቅናቄ ለማድረግ ፣2 መቶ ሺህ በላይ አባላትን ለማፍራት፣ አጠቃላይ ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማሰባሰብ መታቀዱን አቶ ዳንኤል አስረድተዋል ።
ሁሉም ሰው ዘር፣ብሔርና ሀይማንት ሳይለየው የልማት ማህበሩ አባል በመሆን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል ።
ዘጋቢ : ተመስገን አበራ-ከጂንካ ቅርንጫ
More Stories
በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ ተደረገ
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ