የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት የ4ኛ አመት የምስረታ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት የ4ኛ አመት የምስረታ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

ሀዋሳ፡ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት የ4ኛ አመት የምስረታ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻ፣ የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞኖች፣ የወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍል በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የክልሉና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል ።

ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ