የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምርህት መስክ ያሰለጠናቸውን ለ16ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
በምርቃት መርሃ ግብር ላይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጉቼ ጉሌ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ፕሮፌሰር ገብረ ያንትሱ : የወላይታ ሶዶ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 859 ተማሪዎችን አስመረቀ ።
ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ውጤት አምጥተው መመረቃቸውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጉቼ ጉሌ የተናገሩ ሲሆን በሀገር ደረጃ ለሰላም መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ተመራቂዎች ከዩኒቨርስቲ ያገኙት እውቀት በመጠቀም የተሻለ አገር ለመገንባት የሚደረገው ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ ያቀረቡት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ገብረ ያንትሱ ናቸው። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም ወደ ተሻለ ኑሮ ህዝብን ማሻገር ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ :- ፋሲል ሀይሉ
More Stories
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአገራችን አልፎ ለጎረቤት አገራት የብርሃን ምንጭ ከመሆን ባሻገር ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር ነው – አበባዬሁ ታደሰ (ዶ/ር)
ጥንታዊው የካፋ ነገስታት የንግስና ዘውድ እና መቀመጫ ወደ ቀደመ ስፍራው በመመለሱ መደሰታቸውን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ