የህዝቦች አብሮነትና አንድነት የማጠናከር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ

የህዝቦች አብሮነትና አንድነት የማጠናከር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ

`የአባቶች ሚና በልዩነት ለተዋበ ጠንካራ የህዝቦች አንድነት’ በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ አባቶችን ያሳተፈ የምምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ተካሂዷል።

የዚህ መድረክ ዋና አላማ የህዝቦችን አንድነት ማጠናከር ነው ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ ምስረታ ወቅት የሰላም የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነ ጠንካራ ክልል የመፍጠር ግብ ተይዞ እንደነበር አስታውሰው ይህ ግብ እንዲሳካ ትልቁን ድርሻ የሚወጡት የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያያት አስፈልጓል ብለዋል።

ክልሉ ከተመሠረተ በኋላ ክልሉ ትልልቅ ሁነቶችን አሳክተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በየዘርፉ የተያዙ ዕቅዶችን መፈፀም መቻሉን አንስተዋል።

ክልሉ ካለው ዕምቅ አቅም አንፃር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ጥላሁን ክልሉን ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር በተሰሩ ስራዎች ክልሉን የሰላም ተምሳሌት ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲጠናከር ከዚህ በኋላ የሚሰሩ ሰራዎችን የበለጠ ለስኬት እንዲበቁ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በዚህ የውይይት መድረክ ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ