የሴቶችን ግንዛቤ በማሳደግ ከተረጅነት ወደ ምርተማነት በማምራት ከዕዳ ወደ ምንዳ መሸጋገር እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ገለጸ

“በጎነት ለእህትማማችነት፣ ለትውልድ ግንባታ እና ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል ።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደ ሀገር የተያዙ ዕቅዶች መኖራቸውን የተናገሩት በብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መስከረም አበበ ዕቅዱን ከማሳካት አንፃር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዜጎችን ከተረጅነት አስተሳሰብ በማላቀቅ የሀገር ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ በብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ካመቶ ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ ዑመድ ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ሁሉ አቀፍ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት አቅም ማጎልበት ይገባል ብለዋል ።

ዘጋቢ ፡ ሰለሞን አላሶ- ከአርባምንጭ ጣቢያችን