“ምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ሀገራዊ ማንነት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸው ፋይዳን ትልቅ መሆኑን በመወያያ ሰነዱ ላይ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም የጋራ ማንነት ከመገንባት ይልቅ የግለኝነት ትርክት የሚያጎሉ ተግባራት በስፋት ይስተዋሉ ነበር።
ሀገርን በዘላቂነት ለማስቀጠል አንዱ የሌላውን መብት አክብሮ መኖርን እና ሀገራዊ ማንነት ግንባታ ላይ ማተኮር እንደሚገባም ተመላክቷል።
በውይይት መድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መነቴ ሙንዲኖን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ: አብደላ በድሩ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ