የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የምስራቅ ጉራጌ ዞን የልማት፣ የምስረታና የኢንቨስትመንት ፎረም አስመልክቶ በቡታጅራ ከተማ ታላቁን የጎዳና ላይ ሩጫ አስጀመሩ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የምስራቅ ጉራጌ ዞን የልማት፣ የምስረታና የኢንቨስትመንት ፎረም አስመልክቶ በቡታጅራ ከተማ ታላቁን የጎዳና ላይ ሩጫ አስጀመሩ

“ኑ! ለምስራቅ ጉራጌ ዞን ልማት በጋራ እንሩጥ” በሚል መርህ እየተካሄደ በሚገኘው የሩጫ መርሃ-ግብር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ አትሌቶች ተገኝተዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የልማት፣ የምስረታና የኢንቨስትመንት ፎረም በቡታጅራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ መሃመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን