የትራፊክ አደጋን ለመከላከልና ለመቀነስ እንዲሁም የመንገድ ደህንነት ላይ የተሻለ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው
ንቅናቄው ”ከመንገድ ትራፊክ አደጋ እንጠንቀቅ፤ ምትክ የሌለውን የሰው ህይወት እና ንብረት ከጉዳት እንጠብቅ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው።
በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ንቅናቄውን ያዘጋጀው የክልሉ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ነው።
ዘጋቢ: ጀማል የሱፍ
More Stories
በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ወደስራ ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ
በፍየልና በግ ማሞከት ተግባራት ላይ በመሰማራታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን በሀዲያ ዞን አንዳንድ የሶሮ ወረዳ ሴቶች ተናገሩ
የገጠር ተደራሽ መንገድ የበርካቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እየፈታ መሆኑ ተገለጸ