አታላንታ ከ61 ዓመታት በኋላ ዋንጫ አነሳ
የጣሊያኑ እግር ኳስ ክለብ አታላንታ በዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ የጀርመኑን ባየር ሊቨርኩሰንን 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከ61 ዓመታት በኋላ ዋንጫ አንስቷል።
የአታላንታን ሶስቱንም የማሸነፊያ ጎሎች ናይጄሪያዊው አጥቂ አዴሞላ ሉክማን ሲያስቆጥር በዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሃትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል።
በሁሉም ውድድሮች 51 ጨዋታዎችን ሳይሸነፍ ፍፃሜ የደረሰው ባየር ሊቨርኩሰን ከ361 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈት ደርሶበታል።
ሊጠናቀቅ ከጫፍ በደረሰው የውድድር ዘመንም የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ በአንድ ጨዋታ 3 ጎል ሲቆጠርበት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አዘጋጅ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው