የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂና የግብዓት አጠቃቀምን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝ የጋሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጋሞ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 20ኛ መደበኛ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በጉባኤ ላይ ተገኝተው የዞኑን የ6 ወራት ሪፖርት አቅርበዋል።
የአርሶአደሩን የቴክኖሎጂና የግብዓት አጠቃቀምን ለማሳደግ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት አስተዳዳሪው በጤፍ እና በቅመማ ቅመም ምርትና ምርታማነት ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የእንሰሳት ሀብት ልማትን በተመለከተ ከወተት ምርት፣ ከሥጋ ሀብት፣ ከዶሮ ልማት ማሻሻል እንዲሁም ከንብ ማነብ ጋር በተያያዘ በስፋት ተግባራት ተዳሰዋል።
የመኖ ልማት፣ ቆዳና ሌጦ በተመለከተም የተከናወኑ ተግባራትን ለምክር ቤቱ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች አቶ አባይነህ አበራ በስፋት አቅርበዋል።
ከከተሞች የማስፈፀም አቅም ግንባታና አካባቢ ልማት ረገድ፣የቤት ልማትና አስተዳደር፣ ከመሬት መብት ምዝገባና መረጃ ሥርዓት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርኘራይዝ፣ የግብይት ሥርዓትን በተመለከተ በሪፖርቱ ዳሰዋል አስተዳዳሪው።
በሰብል ምርት ቁጥጥር እና በሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች በዞኑ በተከናወኑ ተግባራትና በዕቅዶቹ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ለምክር ቤቱ አባላትና ለተጋባዥ እንግዶች በሪፖርቱ ቀርቧል።
ዘጋቢ፡ ታምሩ በልሁ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የክልሉ መንግስት ከምን ጊዜም በላይ ህዝቡን ለማገልገል ዝግጁ ነው -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ-ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል
ከ19ሺህ በላይ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ወደ ተግባር መግባታቸውን ተገለጸ