በበልግ እርሻ ወቅት ከሚመረቱ ሰብሎች የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ የኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

በበልግ እርሻ ወቅት ከሚመረቱ ሰብሎች የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ የኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

በወረዳው በአዝርእትና በሥራሥር ሰብሎች ከ 6 ሺ 7 መቶ በላይ ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ገልጿል

በዞኑ ኮይሻ ወረዳ በበልግ ወቅት በቆሎ፣ቦሎቄ፣ሰሊጥ፣ካሳቫና ሌሎችም ሰብሎች እንደሚመረቱ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

በወረዳው በዋና ዋና ሰብሎች 6 ሺ 4 መቶ 30 ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ ለመሸፈንና 1 ሺ 7 መቶ 93 ሄክታር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለማምረት ዕቅድ ተይዞ አሁን ላይ 6 ሺ 7 መቶ 36 ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ መሸፈኑን የወረዳው ም/አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ጎበዜ ተናግረዋል።

በ 15 ክላስተር ከ 5 መቶ 80 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 3 መቶ 22 ሄክታር ማሳ ላይ የሰሊጥ ምርት እየለማ እንደምገኝ ተገልጿል።

ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አንጻር 7 መቶ 93 ሄክታር ለማልማት

ታቅዶ 7 መቶ 42 ሄክታር ቴክኖሎጂን በመጠቀም በምርት መሸፈኑን አቶ መስፍን አስረድተዋል።

የወረዳው ግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ ዮናስ አድነው አርሶ አደሮችን በመለየት በቅርበት የድጋፍና ክትትል ስራ እየሠሩ ስለመሆኑን ነው የሚገልፁት።

በወረዳው ኦካሼና ሎሜ ቀበሌ ካነጋገርናቸው አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር በለጠ በቀለ፣ ኤርሚያስ መሀመድና መርኪኔ ማርጮ በበልግ እርሻ በቆሎ፣ሰሊጥና የመሳሰሉ ሰብሎችን በመዝራት እያረሙና እየተንከባከቡ ስለመሆናቸው ነው የሚናገሩት።

ዘጋቢ: ደረጀ ተፈራ – ከዋካ ጣቢያ