የክልሉን የዘጠኝ ወራት የሠላምና ፀጥታ ሥራ አፈፃፀም የሚገመግም መድረክ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ: ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል::

ባለፉት ጊዜያት የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቅ ሥራ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ በየአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ መድረኩ እንደሚያተኩር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገልፀዋል::

የተከናወኑ የሠላምና ፀጥታ ሥራዎችን አፈፃፀም የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እያቀረቡ ሲሆን መድረኩ የዘርፉን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል::

በመድረኩ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳ የፀጥታ መዋቅር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል::

ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ